Fe’fe’ (bafang, nufi)
Le fe'efe'e, aussi souvent appelé nufi, est une langue bamilékée de la région de l'Ouest du Cameroun.Le fe’efe’e, aussi souvent appelé nufi, est une langue bamilékée de la région de l'Ouest du Cameroun.
Source : Wikipedia francophone
አማርኛ ፡ የኢትዮጵያ ፡ መደበኛ ፡ ቋንቋ ፡ ነው ። ሴማዊ ፡ ቋንቋዎች ፡ ውስጥ ፡ የሚመደብ ፡ ሲሆን ፡ ካረቢኛ ፡ ቀጥሎ ፡ ሁለተኛ ፡ ብዙ ፡ ተናጋሪዎች ፡ ያሉት ፡ ቋንቋ ፡ ነው ። በአፍሪካ ፡ ከስዋሂሊ ፡ ቀጥሎ ፡ 3ኛውን ፡ ቦታ ፡ የያዘ ፡ ነው(በተናጋሪ ፡ ቁጥር)። እንዲያውም ፡ 85.6 ፡ ሚሊዮን ፡ ያህል ፡ ተናጋሪዎች ፡ እያሉት ፣ አማርኛ ፡ ከአረብኛ ፡ ቀጥሎ ፡ ትልቁ ፡ ሴማዊ ፡ ቋንቋ ፡ ነው። የሚጻፈውም ፡ በአማርኛ ፡ ፊደል ፡ ነው። አማርኛ ፡ ከዓረብኛና ፡ ከዕብራይስጥ ፡ ያለው ፡ መሰረታዊ ፡ ልዩነት ፡ እንደ ፡ ላቲን ፡ ከግራ ፡ ወደ ፡ ቀኝ ፡ መጻፉ ፡ ነው። የዐምሐራ * ግዛት ፡ ተብሎ ፡ የሚታወቀው ፡ ቦታ ፡ በአሁኑ ፡ መካከለኛና ፡ ደቡብ ፡ ወሎ ፡ እና ፡ ሰሜን ፡ ሸዋ ፡ ይገኝ ፡ እንደነበር ፡ በታሪክ ፡ ይጠቀሳል። ከክርስቶስ ፡ ልደት ፡ በፊት ፡ ከ200 - 130 ዓ.ዓ. ፡ የነበረው ፡ አጋታርከስ ፡ ስለ ፡ ቀይ ፡ ባህር ፡ እና ፡ አካባቢው ፡ ሲጽፍ ፣ ትሮጎዶላይት ፡ ያላቸው ፡ ሕዝቦች – τής Kαμάρ λέξιςα (የካማራ Camàra ቋንቋ) ወይንም ፡ Kαμάρα λέξιςα (ካማራ Camàra ቋንቋ) ይናገሩ ፡ እንደነበር ፡ ዘግቧል። ከዚህ ተነስተው ፡ የተለያዩ ፡ ታሪክ ፡ አጥኝዎች ፡ የአጋታርከስ ፡ ካማራ ፡ ቋንቋ ፡ የአሁኑ ፡ አማርኛ በወር የቋንቋ አባሪና ፡ ወላጅ ፡ እንደሆነ ፡ ያስረዳሉ። ትክክለኛው ፡ አማርኛ ፡ አንዳንዴ ፡ «የንጉሥ ፡ ቋንቋ» ፡ ወይም ፡ ደግሞ ፡ «ልሳነ-ንጉሥ» በመሰየም ፡ ታወቋል። አማርኛ ፡ ልሳነ-ንጉሥ ፡ የሆነው ፡ በ1272 ዓ.ም. ከዛጔ ሥርወ መንግሥት ፡ በኋላ ፡ አጼ ፡ ይኩኖ ፡ አምላክ ፡ ሰሎሞናዊውን ፡ ሥርወ-መንግሥት ፡ መልሶ ፡ ሲያቋቁም ፡ ነበር። አማርኛ ፡ ልሳነ-ጽሑፍ ፡ መሆን ፡ የጀመረው ፡ በ14ኛው ፡ ክፍለ ፡ ዘመን ፡ ላይ ፡ ሲሆን ፡ ይህንንም ፡ ያደረገው ፡ ሁሉንም ፡ የግዕዝ ፡ ፈደላትን ፡ በመውሰድና ፡ 6 ፡ አዳዲስ ፡ የላንቃ ፡ ፊደላትን ፡ (ማለትም ሸ ፣ ቸ ፣ ኘ ፣ ዠ ፣ ጀ ፣ ጨ) እና ፡ ኸን ፡ በመጨመር ፡ ነበር። ነገር ፡ ግን ፡ በጽሑፍ ፡ ይበልጥ ፡ መስፋፋት ፡ የጀመረው ፡ ከአጼ ፡ ቴዎድሮስ ፡ ጀምሮ ፡ ሲሆን ፡ ለእዚህም ፡ በተለይ ፡ አስተዋጽኦ ፡ ያደረገው ፡ ጸሐፊያቸው ፡ ደብተራ ፡ ዘነብ ፡ ነበር። አማርኛ ፡ በተለይ ፡ የተስፋፋው ፡ የዳግማዊ ፡ አጼ ፡ ምኒሊክን ፡ የግዛት ፡ ማስፋፋት ፡ ዘመቻ ፡ ተከትሎና ፡ እንዲሁም ፡ ዘመናዊ ፡ ትምህርት ፡ ኢትዮጵያ ፡ ውስጥ ፡ ከተጀመረ ፡ በኋላ ፡ ነበር። አማርኛ ለብዙ ዘመናት በእጅ ሲጻፍ ቆይቶ በ፲፱፻ ዓ.ም. ገደማ በማተሚያ መሣሪያ ሊከተብ ችሏል። የግዕዝን ፊደል በዶ/ር ኣበራ ሞላ ፈጠራ ወደ ኮምፕዩተር ገብቶ ከ፲፱፻፹ ዓ. ም. ወዲህ በኮምፕዩተር መጠቀም ከመቻሉም ሌላ በዩኒኮድ ዕውቅና ኣግኝቷል። ይህ የተስፋፋ ገጽም የቀረበው በእዚሁ ሥርዓት ሲሆን በቋንቋው የተጻፉ መረጃዎች ቊጥሮች እያደጉ ነው። የዓማርኛ ፊደልና ቋንቋም ዕውቅና እያደገ ስለመጣ በእጅ ስልኮችም በሚገባ ሥራ ላይ እየዋለ ነው። ኣፕል የቋንቋ ገበታዎቹን ሌሎችም እንዲጠቀሙበት በ፳፻፯ ዓ. ም. ስለከፈተ ዓማርኛን እንደሌሎች የዓለም ባለፊደል ቋንቋዎች መርጦ መጠቀም ተችሏል። በ፳፻፰ ዓ. ም. ግዕዝ የመጀመሪያን የኣሜሪካ የባለቤትነት መታወቂያ (ፓተንት) ኣግኝቷል። ይህም የሆነው በየካቲት 10 ቀን 2008 ዓ.ም. አማርኛ ወደ ማናቸውም ሌላ ቋንቋ በኮምፒውተር በቀላሉ ወደሚተረጎሙት ቋንቋዎች ገብታለች። ሆኖም የትርጉሙ ጥራት ከፍ ያለ ሳይሆን ስኅተቶች የተሞላበት ሆኖ ቀርቷል። ዘዬ አማርኛ ቋንቋ ወስጥ አራት ዋና ዘዬዎች አሉ እነሱም የጎንደር፣ የጎጃም፣ የወሎ፣ የሸዋ እና ዘመናዊ አማርኛ ናቸው። ዘየወቹ ብዙም ልዩነት የላቸውም ይህም ማለት ሁለት የተለያየ አማርኛ የሚያወሩ ሰዎች ይግባባሉ ማለት ነው። በመላ ኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት የሚነገረው ዘመናዊ አማርኛ ነው። ዘመናዊ አማርኛ በብዛት በሸዋ አማርኛ ላይ የተመሰረተ ሲሆን የሚለይበት ብዙ ገጸ ባህሪያትም አሉ። ከነዚህ በሃሪያት ውስጥ የሚከተሉት የተወሰኑት ናቸው። ሸዋ አማርኛ ዘመናዊ አማርኛ 'ቀ' እንደ 'ኧ' ሲባል 'ቀ' እንደ 'ቀ' ነው የሚባለው 'ከ' በ'ተ' እና በ'ኸ' ሲባል 'ከ' እንደ 'ከ' ይባላል ከላይ ከተጠቀሱት ምሳሌያት ማየት እንደሚቻለው ከሸዋ አማርኛ በተቃራኒ ዘመናዊ አማርኛ እንደሚጻፈው ነው የሚባለው። በተጨማሪም ዘመናዊ አማርኛ ውስጥ ብዙ የተውሶ ቃላት ይገኛሉ።
Source : Wikipedia local
Alphabets
- alphasyllabaire guèze
- alphabet latin
Codes de langue
Source : Wikidata